Both Teams to Score “ሁለቱም ቡድኖች ጎል ያገባሉ” ግምቶች

[bothTeamToScore]

እንደሚታወቀው ማንኛውም የእግር ኳስ ጨዋታ በሁለት ቡድኖች መካከል ይካሄዳል። እነዚህ እርስ በርስ የሚጋጠሙት ቡድኖች ባለሜዳ ቡድን እና ከሜዳ ውጭ የሚጫወት ቡድን በመባል ይከፈላሉ። የሊግ ውድድር ጨዋታዎች በሚካሄድበት ወቅት በራሱ ሜዳ የሚጫወተው ቡድን ባለሜዳ ቡድን ወይም ሆም ቲም ይባላል። ከሜዳው ውጭ መጥቶ የሚጫወተው ቡድን ደግሞ ከሜዳ ውጭ የሚጫወት ቡድን ወይም አዌይ ቲም ይባላል። እንደ አፍሪካ ዋንጫ (አፍኮን)፣ ዩሮ እና የዓለም ዋንጫ ባሉ የእግር ኳስ ውድድሮች ወቅት ግን ባለሜዳ ቡድን እና ከሜዳ ውጭ የሚጫወት ቡድን የሚለየው በኮምፒዩተር በታገዘ የቀመር ስልት ትንታኔ ላይ ነው፡፡

በአንድ የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ ከመጨረሻ ውጤት አንጻር የሚጠበቁ ሦስት አይነት ምርጫዎች ሲኖሩ፣ እነሱም አንድ፡- ባለሜዳው ቡድን ሊያሸንፍ ወይም ከሜዳ ውጭ የሚጫወተው ቡድን ሊሸነፍ ይችላል፣ ሁለት፡- ባለሜዳው ቡድን ተሸንፎ ወይም ከሜዳ ውጭ የመጣው ቡድን ሊያሸንፍ ይችላል። በመጨረሻም ጨዋታው በእኩል ውጤት ወይም አቻ ለአቻ በሆነ ውጤት ሊያልቅ ይችላል፡፡ የአንድ ቡድን አሸናፊነት የሚወሰነው ቡድኖቹ በሚያስቆጥሯቸው የጎሎች ብዛት ሲሆን፣ በጎል ብልጫ ያለው ወይም ብዙ ጎል ያስቆጠረው ቡድን ጨዋታውን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል፡፡

ሆኖም ሁለቱም ቡድኖች ግብ አስቆጥረው የጎል ብልጫ ልዩነት ከሌላቸው ጨዋታው ያለአሸናፊ ይጠናቀቃል፡፡ በዚህ አጋጣሚ በእግር ኳስ ውርርድ ሜዳ ውስጥ፣ ተወራረጆች ውጤቱን “ሁለቱም ቡድኖች ጎል ያገባሉ” ለሚባለው የውርርድ ምርጫ አመቺ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ይህ የውርርድ አይነት በተለያዩ ስያሜዎች የሚታወቅ ሲሆን አንዳንዴ ቢቲቲኤስ (የስ) እና ቢቲቲኤስ (ኖ) በሚል ምርጫ ይቀርባሉ፤ እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች ላይ ደግሞ ጂጂ (ጎል ጎል) እና ኤንጂ (ኖ ጎል) ተብለው ይጠራሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በታች እንደሚገለፀው የሁለቱም ቡድኖች ጎል የማስቆጠር ውርርድ በጨዋታው ውጤት የቡድኖች መሸናነፍ  ላይ የተመረኮዘ አይደለም።